አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ባለፈው አንድ ዓመት እየሰራንባቸው የቆየነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶች በመቀጠል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ነው ያሉት።
የሃሳብ ልውውጣችን የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻችንን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጣናዊ መረጋጋት እና ልማት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር ብለዋል በመልዕክታቸው።