አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአንጎላ ሉዋንዳ እየተደረገ በሚገኘው 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ በቴኳንዶ 73 ኪሎ ግራም ዮሐንስ ዘለቀ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አምጥቷል።
ዮሐንስ በፍፃሜ ጨዋታ ኮትዲቯራዊውን ተጋጣሚ በመርታት ነው የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣው።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ ስምንተኛ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
በሙባረክ ፋንታው