ስፓርት

ቼልሲ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር አቻ ተለያየ

By Hailemaryam Tegegn

December 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ከሜዳው ውጭ ኒውካስል ዩናይትድን የገጠመው ቼልሲ 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል፡፡

ባለሜዳው ኒውካስል በቮልትማደ ሁለት ግቦች 2 ለ 0 ሲመራ ቢቆይም፥ ቼልሲ በሪስ ጀምስ እና ዦአዎ ፔድሮ ግቦች ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ማንቼስተር ሲቲ ከዌስትሃም፣ ወልቭስ ከብሬንትፎርድ፣ ብራይተን ከሰንደርላንድ እንዲሁም ቦርንማውዝ ከበርንሌይ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር ከሊቨርፑል ምሽት 2 ሰዓት ከ30 የሚገናኙ ሲሆን፥ የሊጉ መሪ አርሰናል ከኤቨርተን እንዲሁም ሊድስ ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት የሚደረጉ የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው፡፡