ስፓርት

የአስቶን ቪላ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ጨዋታ ይጠበቃል

By Yonas Getnet

December 21, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል።

አስቶን ቪላ በውድድር ዓመቱ ድንቅ ብቃት በማስመልከት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ33 ነጥብ ሶስተኛ ላይ ሲሆን ወጥ ብቃት ማሳየት የቸገረው ማንቼስተር ዩናይትድ በ26 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ማንቼስተር ዩናይትድ በጥሩ ቁመና ላይ ከሚገኘው እና በሜዳው ቪላ ፓርክ ከሚጫወተው አስቶን ቪላ ከባድ ፈተና እንደሚገጥመው ይጠበቃል።

ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ በአምስቱ ሲያሸንፍ፤ በአንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።

ትናንት በተደረጉ የሊጉ 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ኒውካስል እና ቼልሲ 2 አቻ ሲለያዩ፤ ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0፣ ሊቨርፑል ቶተንሀምን 2 ለ 1፣ አርሰናል ኤቨርተንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወቃል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!