አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል በደብረሃን ከተማ አምራች ኢዱስትሪዎች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ ጉብኝት እያካሄደ ነው።
ጉብኝቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ ሲሆን፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እና የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ተሳትፈዋል።
እንዲሁም የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በጉብኝቱ ላይ ተገኝተዋል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ አምራች ኢዱስትሪዎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ መመልከትና እያጋጠሟቸው ያሉ ተግዳሮቶችን በቅንጅት ለመፍታት የሚያስችል መፍትሄ ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል።
የጀር አግሮ ኢንዱስትሪ፣ ፌቢላ መኪና መገጣጠሚያ፣ ብሮውን ፉድስ፣ ዴዴ ጠርሙስ፣ ጁኒፐር ግላስ በአምራች ኢንዱስትሪ እየተጎበኙ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ናቸው።
አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ያሉበትን የምርት ሂደትና እያጋጠሟቸው ያሉ ተግዳሮቶችን ለአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስሉ አቅርበዋል።
በዓለምሰገድ አሳዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!