የሀገር ውስጥ ዜና

ጠንካራ ተቋም መፍጠር በሀገር ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ወሳኝ ነው – አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)

By Abiy Getahun

December 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)ጠንካራ ተቋም መፍጠር በሀገር ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ወሳኝ ነው አሉ።

አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ ተቋም ቀጣይነት ያለው እና ጠንካራ መሰረት ላይ የተጣለ መሆን ይኖርበታል፡፡

በቢዝነስ፣ ፖለቲካ፣ ሃይማኖት እና ሌሎችም ዘርፎች ላይ ጠንካራ ተቋም መፍጠር በሀገር ሁለንተናዊ እድገት ውስጥ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ ተቋም ጠንካራ የሚሆነው የተዘረጋ ስርዓት ሲኖረው ነው ብለዋል፡፡

ተቋማት በትውልድ ቅብብሎሽ እየተጠናከሩ መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመው፤ መሻሻል ያለባቸውን በማሻሻል መጓዝ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ትናንት የተጀመሩ ሥራዎችን መሰረት በማድረግ ዛሬን በመገንባት መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

አፍርሶ እንደገና መጀመር ወደ ኋላ ይጎትተናል ያሉት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)፤ እርሾ የሌለው አካሄድ መሄድ የለብንም ብለዋል፡፡

በብርሃኑ አበራ

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- https://www.youtube.com/watch?v=7lEbu7MxFvc