የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያ ፕሬዚዳንት ለሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ መጡ

By sosina alemayehu

December 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀብለዋል።