ፋና ስብስብ

የኢቢሲ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

By sosina alemayehu

December 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ ስርዓተ ቀብር በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር ተፈጽሟል።

አቶ አብዱራህማን ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ነው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

አቶ አብዱራህማን ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት አገልግለዋል።

በተለይም በኦቢኤን እና በኢቢሲ ከሪፖርተርነት ጀምሮ እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በኃላፊነት አገልግለዋል።

ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ደግሞ የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር።

አቶ አብዱራህማን ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ።