የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

December 23, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በዛሬው ዕለት ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀብለው የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።

ይህም በሰላምና መረጋጋት ለአፍሪካ መር መፍትሔዎችና ለንግግር ያለንን የወል ጽኑ አቋም ያሳያል ነው ያሉት፡፡