አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሎንግ ሪቨር አግሮ ኢንዱስትሪ ሼፍ መክብብ ዘውዴን የማይ-ክሽን ብራንድ አምባሳደር አድርጓል፡፡
ከ20 ዓመታት በላይ በዘርፉ ሲሰራ የቆየው ሼፍ መክብብ ዘውዴ “ምርጡ ገበታ” በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በዳኝነት የሚሳተፍ ሲሆን፥ ከማይ-ክሽን ጋር በርካታ ስራዎችን ለመስራት ማቀዱን ተናግሯል።
የሎንግ ሪቨር አግሮ ኢንዱስትሪ የሥራ ኃላፊዎች እንዳሉት፥ ኩባንያው በምግብና ቅመማቅመም ዘርፍ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ እየሰራ ሲሆን፥ ከቅመማቅመም ምርቶች በተጨማሪ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ገበያ ላይ ያሉ ምርቶችን በድጋሚ ከማቅረብ ይልቅ በፈጠራ ይዘት የተሞሉ አዳዲስ ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከሀገር ውስጥ ገበያ በተጨማሪ ምርቶቻቸውን ወደ አሜሪካና ብሪታኒያ እየላኩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ኩባንያው ለሚያከናውናቸው የስራ ማስፋፊያዎች ሼፍ መክብብ ጉልሕ አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው የሥራ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡