አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ11ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ሸገር ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ያሬድ ብሩክ እና ጌታነህ ከበደ አስቆጥረዋል፡፡
ሸገር ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ያሬድ መኮንን ከመረብ አሳርፏል፡፡
በተመሳሳይ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ መደረግ በጀመረው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 እየመራ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን የመሪነት ግብ አቡበከር አዳሙ 30ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
በዚሁ ስታዲየም አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ምድረ ገነት ሽረን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡