የሀገር ውስጥ ዜና

የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር…

By Melaku Gedif

December 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ የመሬት አስተዳደር ሥርዓትን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር የአርሶ አደሩን የብድር አቅርቦት ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው አለ የግብርና ሚኒስቴር፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመሪያ ንቅናቄ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በሚኒስቴሩ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ ትግስቱ ገ/መስቀል እንዳሉት÷ የዲጂታል ኢትዮጵያ ትግበራ አካል የሆነውን የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል፡፡

በዚህ መሰረትም ለአርሶ አደሩ የብድር አቅርቦት ለማመቻቸት በማለም የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አመልክተዋል፡፡

መንግሥት ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት የጀመረውን ጥረት በማሳካት የአርሶ አደሩን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል ነው ያሉት፡፡

በብሔራዊ የመሬት አስተዳደር መረጃ ሥርዓት በ516 ወረዳዎች ከ32 ሚሊየን በላይ ማሳ መመዝገቡንና የመሬት ባለቤትነት ምስክር ወረቀት ተደራሽ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሩ ባስመዘገበው የመሬት መጠንና ሀብት የገንዘብ ብድር እንዲያገኝ የፋይዳ መታወቂያ አስፈላጊ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

ሚኒስቴሩ በቀጣይ ሦስት ወራት 12 ሚሊየን በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ የማሕበረሰብ ክፍሎችን የብሔራዊ መታወቂያ ተጠቃሚ ለማድረግ ግብ አስቀምጦ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የብሔራዊ መታወቂያ ተደራሽነትን መቶ በመቶ ለማድረስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ዋና አስተባባሪ ደጀኔ ገብሬ ናቸው፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!