ፋና ስብስብ

በአማራ ክልል የሚገኙ ቋንቋዎችን ለማልማት እየተሠራ ነው

By Yonas Getnet

December 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ቋንቋዎችን ለማልማት፣ ጥበቃ ለማድረግ እና የአጠቃቀም ሥርዓታቸውን ለማሳደግ እየተሠራ ነው አለ።

በክልሉ የሚገኙ ቋንቋዎች ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ሥርዓትን በተመለከተ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን በባህርዳር ከተማ እየመከሩ ነው።

የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ መልካሙ ጸጋዬ በመድረኩ እንዳሉት፤ ቋንቋዎች ጥበቃና እንክብካቤ የሚፈልጉ ኃብት ናቸው።

የቋንቋዎች የአጠቃቀም ሥርዓት ካልተበጀ ከጊዜ ወደ ጊዜ በውጫዊና ውስጣዊ ተጽዕኖዎች ምክንያት ከማኅበረሰብ ማንነቱ መገለጫነት እየወጡ ሊዳከሙ ይችላል ብለዋል።

ስለሆነም ለቋንቋዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ እንክብካቤና ጥበቃ ለማድረግ የቋንቋ ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ደንብ በማውጣት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ መምህርና ተመራማሪ ማረው ዓለሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ባለሙያዎችን ባሳተፈ መንገድ ለቋንቋዎች እንክብካቤ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የቋንቋዎች አጠቃቀም ችግር በእውቀት ማነስ፣ በውጭ ቋንቋ መሰየምና መጠራት የመፈለግ የተዛባ አመለካከት፣ በግዴለሽነት፣ የተዛባ የቋንቋ አጠቃቀም በሚፈጥሩ ላይ ተጠያቂነት አለመኖር እና በመሳሰሉት የተነሳ እንደሚከሰት አስረድተዋል።

ክልሉ ቋንቋዎችን ለመንከባከብ፣ ለማሳደግ እና የአጠቃቀም ሥርዓት ለማዘጋጀት ከምሁራን፣ ከተቋማት እና ከሌሎች ክልሎች ልምድ በመቀመር የቋንቋዎች ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ደንብ ለማዘጋጀት እየሠራ መሆኑ ተመላክቷል።

በደሳለኝ ቢራራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!