አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል አለ።
የመምሪያው አዛዥ ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ እና የንግስ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው።
ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ጠቁመው፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉና የዋጋ ተመንን እንዲለጥፉ አስገንዝበዋል።
ሕገ ወጥነት እንዳይከሰት ከፍተኛ ቁጥጥር በመደረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መለሰ ቡኑራ በበኩላቸው፤ እንግዶች የሚንቀሳቀሱባቸው መንገዶች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይገጥማቸው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።
የንግስ በዓሉ ታዳሚዎች ወደ ከተማዋ መግባት መጀመራቸውንም ጠቅሰዋል።
በብርሃኑ በጋሻው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!