የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

By Abiy Getahun

December 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ።

ላለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር ሲካሄድ የቆየው የምክር ቤቱ 11ኛ መደበኛ ጉባኤ፤ በዛሬው ዕለት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ የቀረቡ የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ አጽድቋል።

ለምክር ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀላቸው መካከል 4ቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የዘርፍ አስተባባሪዎች ሲሆኑ 9ኙ ደግሞ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች ናቸው።

‎በዚህም መሠረት፦ ‌‎1ኛ, አህመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ፣ ‎2ኛ, ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ፣ ‎3ኛ, ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ፣ ‌‎4ኛ, አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪ፣ ‌‎5ኛ, መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ፣ ‎6ኛ, አቶ ደረጀ ማንደፍሮ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ፣ ‌‎7ኛ, አቶ ጥላሁን ወርቅነህ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣‎ ‎8ኛ, ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ‌‎9ኛ, ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጅ ቢሮ ኃላፊ፣ ‎10ኛ, አቶ አታላይ ጥላሁን የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ፣ ‎11ኛ, ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር) የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ‎12ኛ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እና ‎13ኛ, አቶ ዓባይ መንግሥቴ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሹመታቸው በምክር ቤቱ ጸድቋል።

‎በተጨማሪም ምክር ቤቱ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በአቶ ዓለምአንተ አግደው የቀረቡ 174 የወረዳ ዳኞችን ሹመትም ተቀብሎ ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ተሿሚዎቹ በአመራር ብቃታቸው፣ በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በስራ ልምዳቸውና በስነ ምግባራቸው የተመሰገኑና የክልሉን ሰላም፣ ዕድገትና ልማት ወደፊት ለማሻገር ተግተው ይሰራሉ ተብሎ እምነት የተጣለባቸው እንደሆኑ ተገልጿል።