የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

By Feven Bishaw

August 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው በወረዳው ብርብራ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሞጣ ወደ ግንደ ወይን የሚጓዝ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ዶልፊን) በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡