አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል መሰረተ ልማቶችን በጥራት በማጠናቀቅ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)።
የክልሉ የመሰረተ ልማት ዘርፍ የ5 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል።
አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አዲስ የመሰረተ ልማት ክላስተር በማቋቋምና የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የአስተዳደርና አመራር ሥርዓት አዋጅ በማጽደቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተመራ ነው።
በፌዴራል መንግሥት 150 ቢሊየን ብር የተበጀተላቸው የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተገነቡ እንደሚገኙ ገልጸው÷ ክልሉም ከጠቅላላ በጀቱ 60 በመቶ በላይ ለመሰረተ ልማቶች በሚውል ካፒታል በጀት በመመደብ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት በፌዴራል መንግሥቱና በክልሉ የሚከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየገጠማቸው የሚገኙ ፈተናዎችን በወቅቱ በመፍታት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርግ እንደሆነም አብራርተዋል።
ባለፉት 5 ወራት በመንገድ፣ በቴሌኮም፣ በኃይል አቅርቦት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በመስኖ ልማት፣ በትራንስፖርት መሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱና የክልሉ ጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም መሻሻል ማሳየቱ ተጠቁሟል።
በበጀት ዓመቱ 2 ሺህ 473 ኪ.ሜ መንገድ ለመስራት ታቅዶ በፌዴራል መንገዶች አስተዳደር የሚገነባውን የአስፓልት መንገድ ጨምሮ ባለፉት አምስት ወራት 283 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የሚሸፈን መንገድ መሰራቱ ተመላክቷል።
በደሳለኝ ቢራራ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!