ስፓርት

ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ

By Yonas Getnet

December 29, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አንዋር ሙራድ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 24 ከፍ በማድረግ ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የወላይታ ድቻ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ቀን 9 ሰዓት ላይ መደረግ ጀምሯል፡፡

በተመሳሳይ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ ቀን 10 ሰዓት ላይ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከባህር ዳር ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!