አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታን በካዳስተር ሥርዓት የመመዝገብ ሥራን ለማሳለጥ እየተሰራ ነው አለ የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁን ÷ የመሬት ይዞታን በካዳስተር የመመዝገብ ሥራን ለማቀላጠፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመዘርጋት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
የከተማዋን የመሬት መረጃ በተገቢ ሁኔታ ለመመዝገብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሁሉን አቀፍ የካዳስተር ሥርዓት እውን ለማድረግ እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡
የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኦንላይን አገልግሎት ለመስጠት መትጋት እንደሚገባም ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡
አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከመተግበር ባለፈ ብቁ ክህሎት ያላቸው፣ በሥነ ምግባር የታነጹና ሕብረተሰቡን በታማኝነት የሚያገለግሉ ባለሙያዎችን የማፍራቱ ሒደት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በ337 ቀጣናዎች 291 ሺህ 160 የቁራሽ መሬት መብት እንዲሁም 529 ሺህ 926 የመሬት ይዞታዎች መረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡
ከተረጋገጡ ይዞታዎች ውስጥ 223 ሺህ 586 በቁራሽ መሬት እና በመብት 450 ሺህ 491 የመሬት ይዞታዎች የማረጋገጥ ሒደትን አልፈው ለካዳተር ምዝገባ ብቁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት የስትራቴጂክና ካዳስተር ክህሎት ሥልጠና ያጠናቀቁ 215 ሠራተኞች መመረቃቸውን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
ሠራተኞች የብልጽግና ተምሳሌት በሆነችው አዲስ አበባ የሕዝብ እርካታን ለማረጋገጥ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በሚገባ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ኤጄንሲው የይዞታ ማረጋገጥ፣ የተረጋገጠና አዲስ ይዞታ ምዝገባ፣ የሥመ ንብረት ዝውውር እና የቋሚ ንብረት ምዝገባን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 80 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ መሰራቱ ተመላክቷል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!