አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ዚምባቡዌን 3 ለ 2 አሸንፋለች፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የደቡብ አፍሪካን የማሸነፊያ ግቦች ሞሬሚ፣ ፎስተር እና አፖሊስ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የዙምባቡዌን ግቦች ደግሞ ማስዋንሂሴ እና ሞዲባ (በራስ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ግብጽ እና አንጎላ ያደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።
በምድብ ሁለት ከተደለደሉት መካከል ግብጽ እና ደቡብ አፍሪካ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በምድብ አንድ አዘጋጇ ሞሮኮን ከዛምቢያ እንዲሁም ኮሞሮስን ከማሊ የሚያገናኘው ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!