ቢዝነስ

የኢትዮጵያ ፖስታ የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያና ሳጥን አልባ የመልዕክት አገልግሎት ይፋ አደረገ

By Hailemaryam Tegegn

December 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያና ሳጥን አልባ የመልዕክት አገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡

‌‎የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳግማዊ አልዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ‎ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ደንበኞችን አድራሻ በቀላሉ ማወቅ ያስችላል፡፡

ተቋሙ ላለፉት 132 ዓመታት መልዕክትን በታማኝነት ሲያደርስ መቆየቱን አውስተው፥ አሁን የኢትዮጵያ ፖስታ የዲጂታል ዘመን ላይ ደርሷል ብለዋል። ‎ ‎የቤት ለቤት አገልግሎትን ጨምሮ ደንበኞች በመረጡት አድራሻ መልዕክቶችን ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀበል ይችላሉ ነው ያሉት፡፡ ‎ ‎ከየትኛዉም የውጪ ሀገር ያለምንም ችግር በቨርቹዋል ሳጥን አድራሻ መልዕክቶችን ማስላክ እንዲሁም የሚላኩ መልዕክቶችን የሞባይል ስልክን በመጠቀም መከታተል እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ ‎ ‎አዲሱ አገልግሎት በሀገር ውስጥ የሚላኩ ዶክመንቶች እንዲሁም አነስተኛ ጥቅል መልዕክቶችን መረጃ በየጊዜው በአጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚያሳዉቅ መሆኑንም አስረድተዋል፡። ‎ ‎በሀይማኖት ወንድይራድ‎