አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ሸገር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን ግቦች ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን እና መስፍን ታፈሰ አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 25 ከፍ በማድረግ የሊጉን መሪነት ከፋሲል ከነማ ዳግም ተረክቧል፡፡
በተመሳሳይ ስታዲየም አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ሀዋሳ ከተማን በጫላ ተሺታ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረጉ ጨዋታዎች አዳማ ከተማ ምድረ ገነት ሽረን 1 ለ 0 እንዲሁም ነገሌ አርሲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡