አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን ማሳለጥ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሳካት ጉልህ ሚና አለው አሉ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ እንዳሉት ÷ ዲጂታል የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለማሳለጥ እና ዜጎችን በላቀ ደረጃ ለማገልገል የሚደረገውን ጥረት ያግዛል፡፡
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ መረጃዎች ለዲጂታል የማንነት መታወቂያ ሥርዓት ግንባታና ለፖሊሲ ቀረጻ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም አስረድተዋል፡፡
የምዝገባ ሥርዓቱን በአግባቡ ለመወጣትና የተጀመሩ ጠንካራ ሥራዎችን ለማስቀጠል ባለድርሻዎች ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ሥራን በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በመታገዝ በስኬት ለማጠናቀቅ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በጠንካራ ዲጂታላይዜሽን ሥርዓት የተደገፈ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት ለአስተዳደር፣ ለፍትሕ፣ ለዕቅድና ለልማት የማይተካ ሚና አለው ነው ያሉት፡፡
የሀገርን ደህንነት ለማረጋገጥ እና የዜጎችን ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ጉልህ አበርክቶ እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡
አሁን ላይ ያለውን ከወረቀት ብዙ ያልራቀ አሰራር ሥር ነቀል በሆነ መልኩ ለመቀየርና የተቀናጀ ዘመናዊ የዲጂታል ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
በቅርቡም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው የመመዝገቢያ ሥርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡
በቀጣይ በመላው ኢትዮጵያ ወጥነት ያለውን የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!