አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተወዳጁ ፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 የባለተሰጥዖ ድምፃውያን ውድድር 10ኛ ሳምንት የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።
በዕለቱ ዳዊት ኪ/ማርያም፣ ታፈረ አሰፋ፣ አሮን ኃይሉ፣ አቤል ጌትነት፣ የአብስራ ዘውዱ፣ በሱፈቃድ ገዛኸኝ እና ግዛቸው አማረ በቀጥታ ስርጭት ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
ተወዳዳሪዎቹ ዳኞች ባቀረቡላቸው ሙዚቃዎች ጭምር ይፈተናሉ።
የዕለት አቀራረብን መሰረት የሚያደርገው የፋና ላምሮት ውድድር በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖረዋል።
ይሄን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በፋና በሁለቱም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ በፋና ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በ www.fanamc.com በመከታተል በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ እየተዝናኑ የዳኝነቱ አካል ይሁኑ።
በለምለም ዮሐንስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!