አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና መቻልን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግብ ዲቫይን ዋቹኩዋ አስቆጥሯል።
በተመሳሳይ ቀን 10 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተደረገ ባለው ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1ለ 0 እየመራ ይገኛል፡፡