የሀገር ውስጥ ዜና

በጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ የሚከናወነው የኮሪደር ልማት ትውልዱ በታሪክ እንዲወሳ ያስችላል – አቶ ኦርዲን በድሪ

By Yonas Getnet

December 31, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ትውልዱ በታሪክ እንዲወሳ ያስችላል አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሀረር ከተማ እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኮሪደር ልማቱ የተሽከርካሪና እግረኛ መንገዶች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃዎች፣ የአረንጓዴ ስፍራ እና የመንገድ ዳር መብራት ያካተተ ነው።

አቶ ኦርዲን በድሪ በምልከታው ወቅት እንዳሉት፤ በሀረር ከተማ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ለመጪው ትውልድም መሰረት የሚጥሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

በተለይ በጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ ዙሪያ የቅርሱን ይዘት የጠበቀ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የኮሪደር ልማት ስራው ትውልዱ በታሪክ እንዲወሳ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የልማት ስራው የከተማውን ቀደምት ስልጣኔና እድሜ የሚመጥን እና ለህዝቡ የልማት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ዜጎች የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉባቸው ምቹ የመዝናኛ ስፍራዎች እንዲሟሉ አስችሏል ነው ያሉት።

የህብረተሰቡ ትብብርና ድጋፍ የላቀ ውጤት ከማምጣቱም በላይ ለተጨማሪ ልማት መነሳሳት የፈጠረ መሆኑን ማስረዳታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

የኮሪደር ልማቱ መሰረተ ልማት እንዲሟላ ማስቻሉን እና ለወንጀል መከላከል ስራዎች ውጤታማ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!