አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ከሰንደርላንድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 2ኛ ላይ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ይፋለማል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ሁሉንም በማሸነፍ የበላይነት አለው፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ምሽት 2 ሰዓት 30 ላይ ሊቨርፑል ከሊድስ ዩናይትድ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከፉልሃም ይገናኛሉ፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!