አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራዎች ላይ ዐሻራውን በማኖር ማሕበራዊ ተሳትፎን አጠናክራለሁ አለ ኢትዮ ቴሌኮም።
በተቋሙ የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ቸሩ ጅማ እንዳሉት÷ ሪጅኑ በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በመሳተፍ ዐሻራውን ለማኖር ሳይት ተረክቦ ወደ ስራ ገብቷል።
በክልሉ በኮሪደር ልማት ዘርፍ በተለይ በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ መልሶ ልማት ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው÷ ኢትዮ ቴሌኮምም ከመደበኛ ስራው በተጨማሪ በተለያዩ ማሕበራዊ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ነው ያሉት።
በዛሬው ዕለትም ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ በተጀመረው የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በመሳተፍ ዐሻራውን ለማኖር ሳይት ተረክቦ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ማሕበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
በክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ዳይሬክተር አሚር ረመዳን (ኢ/ር) በበኩላቸው÷ የኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ጥበቃ ስራ ላይ በመሳተፍ ላደረገው አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!