አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከጓደኛዬ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ለፈረንጆቹ 2026 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት በስልክ ተለዋውጠናል ብለዋል፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ያላቸውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ ለመለዋወጥ እና በትብብር ለማስራት መስማማታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!