የሀገር ውስጥ ዜና

የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻልና ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር በቁርጠኝነት ይሰራል – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

By Yonas Getnet

January 02, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት የመንገድ ደህንነትን በማሻሻል በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀልጣፋ የመንገድ ጥገናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው አሉ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ።

ሚኒስቴሩ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ የተለያዩ የክልል መንገድ ተቋማት አዳዲስ ተሽከርካሪዎችንና ሞተር ሳይክሎችን ድጋፍ አድርጓል።

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ድጋፉ መንግሥት የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል፣ ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር እና ቀልጣፋ የመንገድ ጥገናን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል፡፡

ሰፋፊ የመንገድ አውታሮችን የማስተዳደር ሃላፊነት ያላቸውን የክልል መንገድ ተቋማት ፕሮጀክት አፈፃፀም አቅም ለማሻሻል እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

በገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም የገጠሩን ማሕበረሰብ በማስተሳሰር የኢኮኖሚ እድገትን ለማነቃቃት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አውስተዋል፡፡

ድጋፍ ከዓለም ባንክ በተገኘ 220 ሚሊየን ብር ወጪ የተገዙ 28 ሃርድ ቶፕ ተሽከርካሪዎች እና 130 ሞተር ብስክሌቶችን ያካተተ ነው፡፡

በቤዛዊት ከበደ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!