የሀገር ውስጥ ዜና

ያለ ፈቃድ የባንክ ስራ በመስራት ሀገሪቱ ከ41 ሚሊየን ዶላር በላይ እንድታጣ በማድረግ የተጠረጠረው ግለሰብ ተከሰሰ

By Yonas Getnet

January 02, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ውጪ የባንክ ስራ በመስራት ኢትዮጵያ ከ41 ሚሊየን ዶላር በላይ እንድታጣ አድርጓል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት፡፡

ተከሳሹ ፉአድ ተማም በ2017 ዓ.ም ስለ ባንክ ስራ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 1360/2017 አንቀጽ 2 ወይም 6 የተመላከተዉን በመተላላፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል በሚል ክስ ቀርቦበታል።

ተከሳሽ የባንክ ስራን ለመስራት ከብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረዉ በዉጭ ሀገራት የሚገኙ ግለሰቦች ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሲፈልጉ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ያልተያዙ ግብረአበሮቹ ገንዘቡን በመሰብሰብ የሚላክላቸዉን ሰዎች ስም ዝርዝር የባንክ ሂሳብ ቁጥር እና የገንዘቡን መጠን በሚያስተላልፉት መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ በምስክርነት ለቀረቡ 28 ግለሰቦች ማስተላለፉ በክሱ ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም ሕዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም በተለያዩ ቀናት በከፈታቸዉ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች በመጠቀም የባንክ ሂሳቦቹ ከተከፈቱበት ጀምሮ እስከ ሕዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ6 ሺህ 805 ጊዜ ብር 2 ቢሊየን 508 ሚሊየን 19 ሺህ ብር ከዉጭ ሀገራት ገንዘብ ለተላከላቸዉ ግለሰቦች ማስተላለፉ በክሱ ተዘርዝሯል።

ገንዘቡ በባንኮች አሊያም በህጋዊ ገንዘብ አስተላላፊዎች አማካኝነት ወደ ሀገር ቢገባ ኖሮ ሀገሪቱ ልታገኝ የነበረዉን በወቅቱ ገንዘብ ሲሰላ 38 ሚሊየን ዶላር የዉጭ ምንዛሪ እንድታጣ ያደረገ መሆኑን ያመለከተው የዐቃቤ ሕግ ክስ፤ በአቢሲኒያ፣ አዋሽ፣ ብርሃን እና ወጋገን ባንኮች በስሙ በከፈታቸዉ ሂሳብ ቁጥሮች በተለያየ ጊዜ ከዉጭ ሀገር ገንዘብ የተላከላቸዉን ሰዎች ገንዘቡ በህጋዊ መንገድ በህጋዊ ገንዘብ አስተላላፊዎች ወደ ሀገሪቱ ገብቶ ቢሆን ኑሮ ሀገሪቱ ልታገኝ የነበረዉን የዉጭ ምንዛሬ እንድታጣ አድርጓል ብሏል።

በአጠቃላይ ተከሳሹ ከላይ የተጠቀሱትን ባንኮች በመጠቀም 2 ቢሊየን 681 ሚሊየን 489 ሺህ 614 ብር ከዉጭ ሀገራት ገንዘብ ለተላከላቸዉ ሰዎች በማስተላላፍ ገንዘቡ በባንክ አሊያም በህጋዊ ገንዘብ አስተላላፊዎች አማካኝነት ወደ ሀገር ዉስጥ ገብቶ ቢሆን ኖሮ ሀገሪቱ ልታገኝ የነበረዉን ከ41 ሚሊየን 90 ሺህ ዶላር እንድታጣ አድርጓል በሚል ያለ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የባንክ ስራ መስራት ወንጀል ተከሷል፡፡

የክስ መዝገቡን የተመለከተዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ልዩ ወንጀል ችሎት ነዉ፡፡

በመቅደስ ከበደ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!