አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ተግባራዊ ተደርጓል አሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)።
ሚኒስትሩ እንዳሉት፥ ከዚህ ቀደም የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት በማኑዋል ሲሰጥ ከነበረበት ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ስርዓት ተሸጋግሯል።
ይህ የዲጂታል አገልግሎት ማሻሻያ ላኪዎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ያለእንግልት ባሉበት ሆነው እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ተደራሽነትን ከማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል ከመፍጠርና መተማመንን ከማጎልበት አንጻር የጎላ ፋይዳ እንዳለውም ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
የዚህ አሰራር መተግበር በተለይም ከፍተኛ እመርታ በማሳየት ላይ ለሚገኘው ለወጪ ንግድ መሳለጥና ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ማንሰራራት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በቀጣይም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የንግድ ሥርዓቱን ለማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች በሁሉም ረገድ ማከናወን ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ በኦንላይን መሰጠቱ በስትራቴጂው የንግድ ሥርዓቱን የማዘመን ግብ አካል መሆኑንም ተናግረዋል።
በመላኩ ገድፍ