ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ

By Mikias Ayele

January 03, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያተይተዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቴዎድሮስ ሀይለማሪያም ለወላይታ ድቻ እንዲሁም አቤል ያለው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

ቀን 7 ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ እና ፋሲል ከነማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ አቻ መለያየታቸው ይታወቃል።

የሊጉ ጨዋታ ቀጥሎ እየተካሄደ ሲሆን ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገናኙት ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።