የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ከተረጂነት ወጥተዋል

By Hailemaryam Tegegn

January 04, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በምግብ ራሳቸውን በመቻል ከተረጂነት እንዲወጡ ተደርጓል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡

‌‎በአማራ ክልል የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አምስተኛው ምዕራፍ ክልላዊ የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ምርቃት ሥነሥርዓት በዛሬው ዕለት በደብረ ብርሃን ተካሂዷል፡፡

‎የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ እያሱ ኤልያስ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል፡፡ ‎ በአማራ ክልል ያለውን ተፈጥሯዊ ሀብት በመጠቀም መስራት ከተቻለ ክልሉን ሙሉ ለሙሉ ከሴፍትኔት ፕሮግራም ማስወጣት ይቻላል ነው ያሉት፡፡ ‎ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ደረጄ ማንደፍሮ በበኩላቸው፥ በአምስተኛው ምዕራፍ 196 ሺህ 676 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ከሴፍትኔት ፕሮግራም መውጣታቸውን ጠቁመው፥ 630 ሺህ 472 በስራ ላይ የሚገኙ ቤተሰቦች ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገራቸውን ተናግረዋል። ‎ ‎ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል መርህ ዜጎች ከጠባቂነት እንዲላቀቁ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ‎ በኤልያስ ሹምዬ