የሀገር ውስጥ ዜና

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ጋር ተወያዩ

By Adimasu Aragawu

January 05, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴዔታ ሼክ ካሊፋ ቢን አሊ አል ሀርቲን ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

ጌዲዮን (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ በኢትዮጵያና ኦማን መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነትና የጋራ ጥቅም ለማስከበር እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

የኦማን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ እየተከናወነ ባለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠሩ ዕድሎችን እንዲጠቀሙም አበረታትተዋል።

በግብርና እና በግብርና ምርቶች ማቀነባበር፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በቱሪዝም እንዲሁም በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለውን ትብብር ይበልጥ ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሼክ ካሊፋ ቢን አሊ አል ሀርቲ በበኩላቸው÷ ኦማን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው በጋራ ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም የሰላምና የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!