የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች እና በጽሕፈት ቤቱ ለሚደግፋቸው ሕፃናት ማዕድ አጋሩ

By Adimasu Aragawu

January 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚደግፋቸውና ለሚያሳድጋቸው ሕፃናት የበዓል ስጦታዎችን በመስጠት ማዕድ አጋርተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማሕበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባስተላለፈው መረጃ÷ አመራርነት በፖሊሲና በተቋማት ብቻ ሳይሆን በሰብአዊ ግንኙነቶችም ጭምር ይከናወናል ብሏል።

ጽሕፈት ቤቱ ዛሬ በመላው ሀገራችን ቤተሰቦች የገና በዓልን ለማክበር በሚሰናዱበት ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከሚገኙ ሠራተኞች መሀል መገኘታቸውን አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁል ጊዜም በበዓላት እንደሚያደርጉት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤቱ ለሚደግፋቸውና ለሚያሳድጋቸው ሕፃናት የበዓል ስጦታዎችን ሰጥተዋል፣ ማዕድም አጋርተዋል ነው ያለው።

ይኽም በየዕለቱ አስተዋጽኦዋቸው ጎልቶ ባይነገርም ለሀገር የሚያገልግሉ ሠራተኞችን እውቅና የሠጠ፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትም በማሕበረሰባችን ስፍራ እንዳላቸው የሚያሳይ ፍቅርን ያካፈለ ተግባር እንደነበር አመላክተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!