default

የሀገር ውስጥ ዜና

3ኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ተከናወነ

By Yonas Getnet

January 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ 3ኛው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በመስቀል አደባባይ በድምቀት ተከናውኗል።

ዛሬ ቀን 10፡00 ላይ መካሄድ የጀመረው የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በመርሐ ግብሩ ላይ ታድመዋል።