የሀገር ውስጥ ዜና

የአእላፋት ዝማሬ መንፈሳዊ ትዕይንት አስደናቂ ነበረ – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By Adimasu Aragawu

January 07, 2026

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በገና ዋዜማ በመስቀል ዐደባባይ የቀረበው የአእላፋት ዝማሬ መንፈሳዊ ትዕይንት አስደናቂ ነበረ አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ወጣቶች ጨዋነት እና ሥነ ሥርዓት በሞላበት መንገድ ሃይማኖታቸውን መግለጣቸው ስለ መጪው ትውልድ ያለንን አመለካከት የሚቀይር ነው ብለዋል።

ትውልዱ ዕድሉ ከተሰጠው ከአስፈሪና አስጊ ነገሮች ርቆ መልካም የሆነውን መንገድ እንደሚከተል አሳይተዋልም ነው ያሉት።

የሃይማኖት እንቅስቃሴዎች የራስን በመግለጥ፣ ሌላውን በማክበርና የጋራ ዕሴት በመፍጠር ላይ ከተመሠረቱ ለሀገር የሚያስገኙት ዋጋ ከፍ ያለ እንደሆነም አመላክተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!