አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ከሰንደርላንድ እና ቼልሲ ጋር ያደረጋቸውን ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች አቻ የተለያየው ማንቼስተር ሲቲ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 በኢትሃድ ብራይተንን ያስተናግዳል፡፡
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በማሰናበት የ41 ዓመቱን እንግሊዛዊ ሊያም ሮዚኒየር የሾመው ቼልሲ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 በክራቨን ኮቴጅ ፉልሃምን ይገጥማል፡፡
ባሳለፍነው ሰኞ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን ያሰናበተው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ተርፍ ሙር አቅንቶ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 በወራጅ ቀጣናው የሚገኘውን በርንሌይ ይገጥማል፡፡
በሊጉ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች አቻ የተለያዩት ማንቼስተር ዩናይትዶች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ በቀድሞ ተጫዋቻቸው ዳረን ፍሌቸር እየተመሩ ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡
አስቶን ቪላ ከክሪስታል ፓላስ ቦርንማውዝ ከቶተንሃም ሆትስፐር፣ ብሬንትፎርድ ከሰንደርላንድ፣ ኤቨርተን ከወልቭስ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 እንዲሁም ኒውካስትል ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ይጫወታሉ፡፡