አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕጻናት ቅድመ መደበኛ ትምህርት ለኢትዮጵያ ቁልፍ በዘርፉ የተወሰደ የማስተካከያ ርምጃ ነው አለ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፡፡
ቅድመ መደበኛ ትምህርት ሕጻናት በትምህርታቸውና በሕይወታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስፈልጋቸውን ክህሎትና እውቀት በማስጨበጥ ለዘላቂ ትምህርትና ለግል ስኬታማነት መሰረት የሚጥል ነው፡፡
ጥራት ያለው የቅድመ መደበኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት መምህራንን ለማሰልጠን፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ ጠቅሷል፡፡
ለዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ የመዋዕለ ሕጻናት ት/ቤቶች እየተቋቋሙ እንደሚገኙ ነው ያመላከተው፡፡
ቅድመ መደበኛ ትምህርት አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው የማሕበረሰብ ክፍሎች ዘንድ በመድረስ እኩልነትን ያረጋግጣል ያለው ጽ/ቤቱ÷ ማሕበራዊና የአስተሳሰብ እድገትን እንደሚያፋጥን ገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም የሕጻናት ቅድመ መደበኛ ትምህርት የወደፊቱን የሰው ሃይል እንደሚያጠናክር ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያ በእነዚህ የመጀመሪያዎቹ የሕጻናት እድገት ዓመታት ላይ ሃብት በማፍሰስ፣ በራሱ የሚተማመን፣ የበቃ፣ ንቁና ተራማጅ የሆነ ትውልድ በመፍጠር የረጅም ጊዜ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እያሳለጠች እንደምትገኝ ተጠቅሷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!