አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2017/18 ምርት ዘመን በመኸር ከለማው ከ11 ሚሊየን ሔክታር መሬት ውስጥ እስካሁን 9 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ የሰብል ምርት ተሰብስቧል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ በሰሜን ሸዋ ዘን እየተከናወነ የሚገኘውን የምርት አሰባሰብ ሒደት ተመልክተዋል፡፡
አቶ አወሉ አብዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በዘርፉ የተሻሻሉና ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመጠቀም በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረውን ጥረት እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡
በክልሉ በመኸር እርሻ ከ11 ሚሊየን ሔክታር መሬት በላይ በሰብል መሸፈኑን ጠቁመው÷ እስካሁን 9 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ የደረሱ ሰብሎች መሰብሰባቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው ከ368 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ውስጥ እስካሁን ከ270 ሚሊየን ኩንታል በላይ መሰብሰቡን አስረድተዋል።
በክልሉ የምርት ብክነት እንዳይኖር የደረሱ ሰብሎችን በኮምባይነር የመውቃት እና የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በዮሐንስ በቀለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!