አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተወዳጁ ፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 የባለተሰጥዖ ድምፃውያን ውድድር 11ኛ ሳምንት በነገው ዕለት ቀጥሎ ይካሄዳል።
በዕለቱ ዳዊት ኪ/ማርያም፣ ታፈረ አሰፋ፣ አሮን ሀይሉ፣ አቤል ጌትነት፣ በሱፈቃድ ገዛኸኝ እና ግዛቸው አማረ በቀጥታ ስርጭት ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
ተወዳዳሪዎቹ በተመልካች የሙዚቃ ምርጫዎች ይወዳደራሉ።
የዕለት አቀራረብን መሰረት የሚያደርገው የፋና ላምሮት ውድድር በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖረዋል።
ይሄን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት ነገ ቀን ከ6:00 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሁለቱም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ በፋና ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾች፣ በፋና ዩቲዩብ እና በ www.fanamc.com ይከታተሉ።
እንዲሁም በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ እየተዝናኑ የዳኝነቱ አካል ይሁኑ።