ስፓርት

ሴኔጋል ወደ ግማሽ ፍጻሜው ገባች

By Mikias Ayele

January 09, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ሴኔጋል ማሊን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ገብታለች።

ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሴኔጋል ኒጃይ ባስቆጠረው ግብ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በቅታለች።

በጨዋታው የማሊው ቢሱማ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

መርሐ ግብሩ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ አዘጋጇ ሞሮኮ እና ካሜሩን የሚያደርጉት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ይጠበቃል።

ሞሮኮ ታንዛኒያን በማሸነፍ እንዲሁም ካሜሩን ደቡብ አፍሪካን በማሸነፍ ነው ለሩብ ፍፃሜ የደረሱት።