አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ቀን 10፡00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ዘላለም አባተ እና አቡበከር አዳሙ ከመረብ ጋር አገናኝተዋል።
የዕለቱ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ መድን ይጫወታል።
በሊጉ ቀደም ሲል በተካሄዱ ጨዋታዎች ባሕር ዳር ከተማ መቻልን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና 0 ለ 0 ተለያይተዋል።