አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሃላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ሴራ” በሃላባ ቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ ከማለዳ ጀምሮ በሃላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የብሔረሰቡ ተወላጆች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በአዲስ አበባ፣ ሆሳዕና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ እና ዱባይ ሲከበር የቆየው በዓሉ የማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት ዛሬ በሃላባ ቁሊቶ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል።
በበዓሉ የሃላባ ዞን ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፍቶ ጉብኝት ተደርጓል።
በተጨማሪም የሃላባ ዞን አስተዳደር ህንፃ፣ የሃላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ እና ሌሎች የመሠረተ ልማት ስራዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰውን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው