አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አንግለር ፊሺንግ የጥቃት አይነት በዋናነት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ አጥቂዎች ራሳቸውን እንደ ደንበኛ አገልግሎት ሰጪ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ በመምሰል ተጠቃሚዎችን ያጠምዳሉ።
ጥቃቱ የሚጀምረው አጥቂዎች እንደ ባንክ፣ የቴሌኮም ድርጅት ወይም የታወቁ የንግድ ተቋማትን ትክክለኛ ገጾች በመከታተል ነው።
አንግለር ፊሺንግ ስያሚውን ያገኘው አንግለርፊሽ ከተባለውና በዋናነት በጥልቅ ባሕር ውስጥ የሚኖር እጅግ አስገራሚና አስፈሪ መልክ ያለው የዓሣ ዝርያ ነው።
👉ጥቃቱ እንዴት ይፈጸማል? 1. ክትትል፡- አጥቂዎች ታዋቂ የሆኑ ባንኮች፣ የቴሌኮም ኩባንያዎች ወይም የንግድ ተቋማት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይከታተላሉ።
2. ኢላማ መለየት፡- አንድ ደንበኛ በድርጅቱ ገጽ ላይ ቅሬታ ሲጽፍ ወይም እርዳታ ሲጠይቅ
ለምሳሌ፡- “ATM ካርዴ አልሰራም” ወይም “ኢንተርኔት ተቋርጦብኛል” አጥቂዎቹ ወዲያውኑ ያዩታል።
3. መመሰል፡- አጥቂዎቹ የድርጅቱን ትክክለኛ ስም እና አርማ በመጠቀም የሐሰት አካውንት ይፈጥራሉ።
4. ተግባቦት፡- ለደንበኛው በግል መልዕክት ወይም በኮሜንት “ችግርዎን ለመፍታት እንርዳዎ፣ እባክዎ በዚህ ሊንክ መረጃዎን ይሙሉ” በማለት ምላሽ ይሰጣሉ።
5. መረጃ መስረቅ፡- ደንበኛው ሊንኩን ሲጫን ወደ ሐሰተኛ ገጸድር ይወሰዳል፤ እዚያም የባንክ መረጃውን ወይም የሶሻል ሚዲያ የይለፍ ቃሉን እንዲያስገባ ተደርጎ መረጃው ይዘረፋል።
መረጃውን ያገኘነው ከኢንፎርሜሽን ደሕንነት አስተዳደር ነው