የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአርባ አራት ቤቶችን እድሳትን በዛሬው ዕለት አስጀመሩ

By Tibebu Kebede

August 22, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአርባ አራት ቤቶችን እድሳትን በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ቦሌ ርዋንዳ ልዩ ስሙ ጃፖን አልፋ መንደር የሚገኙ አርባ አራት ቤቶች እድሳትን ነው ያስጀመሩት፡፡

የቤቶቹ እድሳት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ለነዋሪዎቹ ንጹህ ውሃን ጨምሮ የመብራት እንዲሁም የመጸዳጃ ቤት እንደ አዲስ የሚደራጁ ይሆናል፡፡

በዚህ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ የአቅመ ደካሞችን ህይወት የሚለውጡ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እስካሁን ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች እድሳት ተከናውኗል፡፡

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከእድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በኋላ ችግኝ መትከላቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡