የሀገር ውስጥ ዜና

የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን ማልማት የሰርክ ተግባራችን መሆን አለበት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Hailemaryam Tegegn

January 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን በሁሉም መልክ ማልማት የሰርክ ተግባር ሊሆን ይገባል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የአካባቢ ጥበቃ ስርዓታችን ደካማ በመሆኑ በድጋሚ ለመተካት እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን ለም አፈራችንን ስናጣ ቆይተናል ብለዋል።

በህዝብና በመንግስት ትብብር የተጀመረው የአካባቢ ጥበቃ ሥራ የዝናብ ወራት ከመቃረቡ በፊት በዚህ መልክ መጀመሩ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አመልክተዋል።

የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን በሁሉም መልክ ማልማት የሰርክ ተግባራችን ይሁን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡