የሀገር ውስጥ ዜና

ዘላቂ ሰላምና ብልጽግናን እውን ለማድረግ እንሰራለን – አቶ አረጋ ከበደ

By Mikias Ayele

January 15, 2026

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ የግጭት እና የድህነት አዙሪትን ሰብረን በመውጣት ዘላቂ ሰላምንና ብልጽግናን እውን ለማድረግ እንሰራለን አሉ፡፡

‘ሰላምን ማጽናት፤ ፀጋን ለማልማት’ በሚል መሪ ሀሳብ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከኢዜአ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

አቶ አረጋ ከበደ በመድረኩ እንዳሉት÷ ክልሉን ካጋጠመው ተከታታይ ግጭትና የድህነት አዙሪት በማላቀቅ ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማምጣት በውይይትና በምክክር ለችግሮች መፍትሔ መፈለግ ይገባል፡፡

ከግጭት አዙሪት በመውጣት ዘላቂ ብልጽግናን እውን ለማድረግ በጋራ መረባረብ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

የውስጥ ጠላቶች ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመተባበር ልማት ላይ ትኩረት የማያደርግ ሥርዓት እንዲገነባ የያዙት ተልዕኮ እንዲከሽፍ ልሂቃኑ የመፍትሔው አካል መሆን አለባቸው ብለዋል።

በመድረኩ ሀገራዊ የምክክር ሂደር፣ የሰላም ግንባታ፣ የአማራ ክልል የመልማት ተስፋዎች፣ የህዝብ ተጠቃሚነት፣ የክልሉ ፀጋዎች እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ቀርበው ውይይቶች እየተደረገባቸው ነው።

በደሳለኝ ቢራራ