አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ14 ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።
የደቡብ ሱዳን፣ ጣልያን፣ ሞሪሺየስ፣ ዛምቢያ፣ ጀርመን፣ ጆርዳን፣ ኒውዝላንድ፣ ቡሩኪና ፋሶ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ ቤላሩስ፣ ፊሊፒንስ፣ የኪርጊስታን እና የላቲቪያ አምባሳደሮች ናቸው የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንቱ ያቀረቡት።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው እንዳሉት፤ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡ ሀገራት መካከል 11ዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ነው።
አምባሳደሮቹ ከፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ጋር ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም በንግድ እና ኢንቨስትመንት በሚሰማሩባቸው መስኮች ላይ መወያየታቸውንም አመልክተዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሚያስከብሩ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ማድነቃቸውን ጠቁመው፥ ሀገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ልምድና ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን አንስተዋል።
በኢትዮጵያና በሀገራቱ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ነው ያሉት።